አስተምህሮ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ከሁሉ አስቀድመን ምስጋና የባህሪው ለሆነው አምላካችን ምስጋናን እናቀርባለን፡፡ በሥራችንም ሁሉ ይረዳን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ እንዲሆንልንም ዘወትር በፊቱ እንቆማለን፡፡

አስተምህሮ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ የጡመራ መድረክ ዛሬ ህዳር 21 ቀን 2010 ዓ.ም ተመሠረተች፡፡ የጡመራ መድረኳ ስያሜ ‘አስተምህሮ’ እንደመሆኑ በዚህ የመጀመሪያው ጡመራችን አስተምህሮ የሚለውን ቃል ትርጉም በአጭሩ እንመለከታለን፡፡ አስተምህሮ የሚለው ቃል ሁለት ዓይነት ትርጉም አለው፡፡

አንደኛ፤ አስተምህሮ ማለት የትምህርት አሰጣጥ ሥርዓት ማለት ሲሆን ይህም የትምህርቱን ይዘት፣ የይዘቱንም ምንጭ፣ የትምህርቱን አሰጣጥ ስልት፣ የመምህራኑና የተማሪዎቹን መስተጋብር ወዘተ… ያጠቃልላል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ከሚገለፅባቸው መንገዶች መካከልም የአደባባይ ስበከት (ለምዕመናን የሚሰበከው)፣ የወንበር ትምህርት (በአብነት ትምህርት ቤት የሚሰጠው) ፣ ልዩ ስልጠናና (በኮርስ መልክ የሚሰጠው ትምህርት) በመገናኛ ብዙሀን (በጋዜጣ በመጽሔት በድረ ገፅ) የሚሰጡት ትምህርቶች ይገኙበታል፡፡

ሁለተኛ፤ መሐረ ማለት ይቅር አለ ማለት ሲሆን፤  አስተምሕሮ ማለት ይቅርታ መጠየቅ /ምልጃ/ ማለት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ስለ ልጆቿ ይቅርታ የምትጠይቅበት፤ ምዕመናንንም ስለ በደላቸው ይቅርታ የሚጠይቁበት፤ ስለዚህም በስፋት ትምህርት የሚሰጥበት ዘመንም ዘመነ አስተምሕሮ ይባላል፡፡ በቤተ ክርስተያናችን የዘመን አቆጣጠር /አከፋፈል/ መሠረት ከኀዳር 6 ጀምሮ እስከ ታኀሣሥ 13 ድረስ ያለው ወቅት ዘመነ አስተምሕሮ ይባላል፡፡

አስተምህሮም በይዘቷ በመጀመሪያው ላይ በማተኮር ለአንባቢያን ይበጃሉ ይጠቅማሉ ያልናቸውን ትምህርቶችንና ወቅታዊ መረጃዎችን የምናደርስባት አዲስ የጡመራ መድረክ ናት፡፡ በዘመነ አስተምህሮ ስለተመሠረተችም ስያሜዋን “አስተምህሮ” ብለናታል፡፡ ለሁላችንም መልካም የአገልግሎት ዘመን እንዲሆንልን በጸሎታችሁ እንድታስቡንና ገንቢ አስተያየታችሁንም በማጋራቱ በኩል እንዳትለዩንም በትህትና እንጠቃለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

1 thought on “አስተምህሮ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s