“ቤት-“ ማለት “ማደሪያ” ማለት እንደሆነ ሁሉ ቤተክርስቲያን የሚለውም የክርስቶስ ማደሪያ ማለት ነው፡፡ እያንዳንዱ ክርስቲያን የክርስቶስ ማደሪያ ስለሆነ ቤተክርስቲያን ይባላል፡፡ ይህም በዋናነት የአንድ ክርስቲያንን ክርስቲያናዊ ሕይወትን ነው የሚመለከተው፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያን ሲባል የሚወክለው ምእመናንን ነው፡፡ ክርስቲያኖች የክርስቶስ ማደሪያዎች ናችውና፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያን ማለት የክርስቶስ ማደሪያ የሆኑ ክርስቲያኖችን /የክርስቲያኖችን ሰውነት/ የሚያመለክት ነው፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ “የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።” 1ኛቆሮ. 3፡16-17 ገላ 1፡13 እንዲሁም የእግዚአብሔር እርሻ ናችሁ፤ የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ፤ ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና። 1ኛቆሮ.3÷9 በራዕየ ዮሐንስም እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል። ራዕ 3÷20 ይላል፡፡ እነዚህ የሚገልጹት እያንዳንዱ ክርስቲያን የክርስቶስ ማደሪያ (ቤተክርስቲያን) መሆኑን ነው፡፡
በጣም አስተማሪ ነው ቤተክርስቲያን ተብሎ የተጠሩ እነማን ናቸው?
LikeLike